Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፣የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች የጋራ  የምክክር መድረክ  በላሊበላ  ከተማ  እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፣የክልሎችናየሁለቱ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች የጋራ  የምክክር መድረክ  በላሊበላ  ከተማ  እየተካሄደ ነው ።

በላሊበላ ከተማ እተካሄደ ባለው የፌዴራል ፣ የክልልና ከተማ  አስተዳደር ምክር ቤቶች የጋራ የምክክር መድረክ ላይ አዲሱ የመንግስታት ግንኙነት አዋጅና  በኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተጀመረውን  የሪፎርም ሥራ ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያዝ ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል ።

በመድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ፣የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም የክልሎች አፈ ጉባኤዎች መገኘታቸውን ከምክር ቤቶቹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ጠዋት ላይ በነበረው ውይይት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ምክትል ዋና ፀሐፊ ዶክተር ሄኖክ ስዩም አማካይነት በቀረበው የምክር ቤቱ የ5 ዓመታት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ላይ ተወያይቷል፡፡

ጉባዔውን የላልይበላ ከተማ ከንቲባ አቶ ይልማ መርቅ በንግግር የከፈቱት ሲሆን፤ ከንቲባው ይህ ጉባዔ በላልይበላ ከተማ በመደረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞም፤ ለመላው የጉባዔው ተሳታፊዎች ወደ ላልይበላ ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል፡፡

ጉባዔውም ሀገሪቱ ታላቅ ድል ባስመዘገበችበት ማግስት የሚካሄድ በመሆኑ ልዩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎ ባደረጉት ንግር ሁለቱ የፌዴራል ምክር ቤቶች ባለፉት የለውጥ ዓመታት ስኬታማ ስራ ማከናወናቸውን በመግለፅ ስብሰባም ውጤታማ እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.