ደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ በአጣዬ እና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች ግምቱ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ አካላት በአጣዬ እና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች ግምቱ ከ4ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ድጋፍ አደረገ።
ለተለያዩ የህክምና አገልግሎት የሚውሉ መድሀኒቶች ፣ ኮምፒዩተሮች፤ ወረቀቶች እና አልባሳት እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
የደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ባዩ ጌታሁን÷ ዩኒቨርስቲው ከዚህ ቀደም በተለያዩ መሰል ድጋፎች ሲሳተፍ መቆየቱን አስታውሰው÷ በቀጣይም ባለው አቅም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ከተማሪዎች የተሰበሰበውን አልባሳት እና የጥሬ ገንዘብ በተወካይነት ያስረከቡት የዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት ያሬድ ብርሀነ÷ ድጋፉ በአካባቢው ተከስቶ በነበረው ግጭት ለተጎዱት ተማሪዎች ከቁርሳቸው ቀንሰው ያሰባሰቡት እንዲሁም አልሳባቱ ከተማሪዎች በጎ ፈቃድ የተነገኘ መሆኑን ተናግረዋል።
የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ አገኘሁ መክቴ÷ የአጣዬ ከተማን ወደ ቀደመ እንቅስቃሴ ለመመለስ በአካባቢው ያሉ ተቋማት የዩኒቨርስቲውን ፈለግ መከተል ይገባቸዋል ብለዋል
አያይዘውም የዩኒቨርስቲው ድጋፍ መሠረታዊ ችግሮችን ሊቀርፍ የሚችል መሆኑንም ገልፀዋል።
በኤልያስ ሹምዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!