Fana: At a Speed of Life!

ጀርመን ለኢትዮጵያ የ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የድጋፍ ማዕቀፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጀርመን ለኢትዮጵያ የ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የድጋፍ ማዕቀፍ ይፋ ማድረጓን የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ጀርድ ሙለር አስታወቁ።

የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ጀርድ ሙለር፥ ጀርመን በዚህ አስቸጋሪ በሆነው ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን በመሆን አጋርነቷን የምታሳይ መሆኑን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አይመድ ገልፀዋል።

በዚህም የጀርመን መንግስት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመቀነስ የ120 ሚሊየን ዩሮ ወይም የ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የድጋፍ ማእቀፍ ይፋ አድርጓል።

የገንዘብ ድጋፉ በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት፣ በጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን የስራ እድል ለመጠበቅ የሚውል መሆኑን ታውቋል።

በተጨማሪም ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያ የህክምና መሳሪያዎች ግዢ የሚውል መሆኑም ተገልጿል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.