Fana: At a Speed of Life!

42 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 42 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከሊባኖስ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ፡፡
ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ የተደረገው ግሎባል አሊያንስ ከተሰኘ በኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ከተመሰረተ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው፡፡
የግሎባል አሊያንስ ተወካዮችም በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ግሎባል አሊያንስ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም 90 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.