Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ አብያተክርስቲያናትን እና ገዳማትን ተመለከቱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ አብያተክርስቲያናትን እና ገዳማትን ተመልክተዋል።
 
ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር የሰላም ሚኒስተሩ ብናልፍ አንዱዓለም፣ ከፍተኛ የጦር ጀኔራችና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላን ተመልክተዋል።
 
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በቅድስቲቱ ከተማ ላልይበላ በነበረበት ወቅት በነዋሪዎች ላይ በደሎችን ሲፈፅም እንደነበር ተገልጿል።
 
የገዳማቱንና አብያተክርስትያናቱን አገልጋይ ካሕናትንም ልብሰ ተክሕኖአቸውን በማስወለቅ ያንገላቷቸው እንደነበር አሚኮ ዘግቧል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.