አማራ ክልልን ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ጎብኚዎች 2 ቢሊየን 445 ሚሊየን 9 ሺህ 550 ብር ገቢ መገኘቱን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ክልሉን ከ5 ሚሊየን 914 ሺህ በላይ ሰዎች መጎብኘታቸውን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡
በክልሉ ያጋጠመው የጸጥታ ችግር በቱሪዝም እንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን የገለጸው ቢሮው÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በዕቅድ የተያዙ ተግባራትን በሚፈለገው ልክ መፈጸም አለመቻሉን አስታውቋል፡፡