Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ለሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባወጡት መልዕክት በራሳቸው እና በመላው ኢትዮጵያውያን ስም እንኳን ወደ ሁለተኛ ሀገርዎ መጡ ብለዋቸዋል።
 
የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ያላቸውን ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር እንደሚያደንቁ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ሁለቱ ህዝቦች በየትኛም ሁኔታ እንደማይነጣጠሉ ተናግረዋል።
 
ለሀገራቱ እና ለህዝቦቻቸው ተጠቃሚነት ሲሉም ይህንን ግኑኝነት ለመጠበቅ ብሎም የበለጠ ለማጠናከር ጥረት እንደሚያደርጉም አረጋግጠዋል።
 
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ዛሬ ነበር አዲስ አበባ የገቡት።
 
በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ከመንግስት ከፍትኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.