Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዓመታዊ የባህላዊ ስፖርቶች ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዓመታዊ የልዩ ልዩ ባህላዊ ስፖርቶች ውድድር በአሶሳ ከተማ ተጀመረ፡፡

በውድድሩ ትግል፣ በ12 እና 18 ጉድጓድ ገበጣ፣ ኩርቦ፣ ቡብ እና ሻህ የተሰኙ ባህላዊ ስፖርቶች እንደሚያካትት የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ትዕዛዙ ታዬ በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ ገልጸዋል፡፡

ዓላማው በሃገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የባህል ስፖርት ውድድር ክልሉን የሚወክሉ ምርጥ ስፖርተኞችን ለይቶ ለማዘጋጀት እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

የክልሉ ስፖርት ኮሚሽነር አቶ በአዱልሙኒዬም አደም ÷ስፖርት ባህላዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅ ያግዛል ብለዋል፡፡

ባህላዊ ስፖርቶች ይበልጥ እንዲለሙ ኮሚሽኑ ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቁመው ፤ ተወዳዳሪዎች በጨዋነት በመሳተፍ ለስፖርቱ እድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ውድድሩ እስከ ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም. እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.