Fana: At a Speed of Life!

የሰራተኞችን መብቶች የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰራተኞችን ጥቅምና መብቶች የማስከበር እንዲሁም ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ካሣሁን ፎሎ ዓለም አቀፉን የሠራተኞች ቀን በማስመልከት የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የሰራተኛውን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ በየጊዜው የሚነሱ ጥያቄዎችን በጥናት ላይ ተመስርቶ ምላሽ እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናግረዋል።

የሰራተኞችን ጥቅምና መብቶች የማስከበር እንዲሁም ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲረጋገጥ፣ የሥራ ላይ ደህንነት፣ መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የላቀ ብቃትና እውቀት፣ ክህሎትና ሁሌም ዝግጁነት ያለው ሠራተኛ የማፍራት ስራም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ካሣሁን ፎሎ በበኩላቸው÷ የሠራተኞች መሰረታዊ ጥያቄዎች በሂደት ምላሽ እንዲያገኙ ከመንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በየአመቱ ሚያዝያ 23 ቀን የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን በነገው እለት በኢትዮጵያ ለ49ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ135ኛ ጊዜ ይከበራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.