Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንቅስቃሴን ገበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የበጋ መስኖ የስንዴ ልማት እንቅስቃሴን ጎበኙ።
ጉብኝቱ እየተካሄደ ያለው በሐዋሳ ዙሪያና ሎካ አባያ ወረዳዎች በአርሶ አደሮችና በባለሃብት በለማ 138 ሄክታር የስንዴ ማሳ ላይ ነው።
ከሁለት ወር በፊት የለማው ስንዴ በአሁኑ ወቅት በጥሩ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ መስፍን ቃሬ በጉብኝቱ ወቅት ገልጸዋል።
በበጋ መስኖ የለማው ስንዴ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለአጨዳ እንደሚደርስ የተናገሩት ኃላፊው ፥ በሄክታር በአማካይ 40 ኩንታል ምርት እንደሚገኝ ይጠበቃል ብለዋል።
በአርሶ አደሮችና በባለሀብት በበጋ መስኖ በስንዴ የለመውን ማሳ የሲዳማ የክልል ምክር ቤት የግብርና ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላትና የሁሉም ዘርፍ ቢሮዎች የስራ ኃላፊዎች እየጎበኙ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.