አቶ አሻድሊ ሀሰን የ”ጽዱ ኢትዮጵያ” ንቅናቄን ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን 15 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ የ“ጽዱ ኢትዮጵያ” ንቅናቄን ተቀላቀሉ፡፡
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ጽዱ፣ ውብ፣ ለጎብኚ ፍሰትና ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን የተጀመረውን ንቅናቄ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው አቶ አሻድሊ ያረጋገጡት፡፡
ንቅናቄው ሰዎች በየመንገድ ዳሩ ከመጸዳዳት ወጥተው ንጽህናውን በጠበቀ ቦታ የመጸዳዳት ባህላቸውን እንዲያሳድጉ፣ ለዚህ ደግሞ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎች እንዲሠሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ መሆኑ ይታወቃል።
ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር 1000623230248 ድጋፍ በማድረግ ንቅናቄውን መቀላቀል ይችላሉ፡፡