Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የመሬት ቀን ለ52ኛ ጊዜ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 52ኛው የዓለም የመሬት ቀን ፕላኔታችንን ለመጠበቅ ‘ኢንቨስት’ እናድርግ” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
የዓለም የመሬት ቀን አካባቢን መጠበቅ፣የተጎዱ ብዝሃ ሕይወቶችን ዳግም ወደ ነበሩት መመለስና ዘላቂነት ያለው ሕይወት መኖር አስፈላጊ መሆኑን ለማስታወስ በየዓመቱ ይከበራል።
የዓለም የመሬት ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው እኤአ ሚያዝያ 22 ቀን 1970 ነበር.።
ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት መዛባት የምታደርገውን ምላሽ አጠናክራ ቀጥላለች።
በዚህም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 18 ቢሊየን ችግኝ መትከል ችላለች፡፡
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በፈረንጆቹ 2019 ላይ በ4 ዓመታት ውስጥ 20 ቢሊየን ችግኞን ለመትከል ታቅዶ የተጀመረ ነው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.