Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ 5ኛው የጋራ የፖለቲካ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የስዊዘርላንድን የቆየ ሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብርን በአዳዲስ የተመረጡ መስኮች ለማሳደግ የሚያስችል የጋራ የፖለቲካ ምክክር በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በምክክሩ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ÷ በተለይም በንግድ፣ በልማት ትብብርና በሰብዓዊ ድጋፍ ረገድ ስዊዘርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት አድንቀዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን÷ ህወሓት ጦረኛ ኃይል ሆኖ እንዲቀጥል መፈቀድ እንደሌለበት ጠቁመው፥ በሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት በትብብር መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

አንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ሂደት በሙሉ ልብ መደገፍ እንዳለበት፣ ተወዳዳሪ የሰላም ሂደቶች እንዲጀምር የሚሉ ወገኖች ከድርጊታቸው ተቆጥበው የተጀመረውን ጥረት ማገዝ እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡

የስዊዘርላንድ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሪ ዋልት በበኩላቸው÷ ስዊዘርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ግንኙነት ልዩ ቦታ እንደምትሰጥ ጠቅሰዋል።

አገራቸው ከሰሃራ በታች ለሚገኙ የአፍሪካ አገራት ባዘጋጀችው ስትራቴጂ የበለጠ ትስስር ለማድረግ ከለየቻቸው ዘጠኝ “ባለ አንበሳ ኢኮኖሚ” አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን አንስተዋል፡፡

ስዊዘርላንድ እ.ኤ.አ ጥር 1 ቀን 2023 ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና የምታገለግል በመሆኑ ኢትዮጵያ በፀጥታው ምክር ቤት በነበረችበት ወቅት የነበራትን ተሞክሮ አካፍላለች፡፡

የስዊዝ ወገንም ለልምድ ልውውጡ ምስጋናውን ማቅረቡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.