Fana: At a Speed of Life!

የህብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ የንቅናቄ መድረክ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ የንቅናቄ መድረክ “ጠንካራ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ለማይበገር የጤና ስርዓት ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ንቅናቄው በዓለምና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ስጋቶችን ቀድሞ በማሳወቅ የጋራ ምላሽ ለመስጠት አስቻይ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ በአንድ ማዕከል ምላሽ የመስጠት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ነው ሚኒስትሯ ያመላከቱት።

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ ያስጀመሩት ይህ ንቅናቄ ስኬታማ ይሆን ዘንድ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት አበርክቶ ይጠይቃል ነው ያሉት።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር ሙስጠፌ መሀመድ በበኩላቸው÷ ንቅናቄውን ለማሳካት ጠንካራ የፋይናንስ ድጋፍ ሊኖር እንደሚገባ አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ÷ በሀገሪቱ ባለፉት አምስት አመታት ወባን፣ ኩፍኝና ኮሌራን በመከላከል ረገድ አበረታች ስራ መሰራቱን ጠቅሰዋል።

ንቅናቄው ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበትና ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ ለሚከሰቱ አደጋዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አላማው ማድረጉንም አንስተዋል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.