Fana: At a Speed of Life!

የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ቤንዚን በሊትር 57 ብር ከ05 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም እንዲሁም ኬሮሲን በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሌሎች የነዳጅ ውጤቶች ማለትም የአውሮፕላን ነዳጅ ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣና ከባድ ጥቁር ናፍጣ ባሉበት እንዲቀጥሉ መወሰኑን ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

መንግስት የነዳጅ ውጤቶችን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እስከ ግማሽ ሲደጉም የቆየ ቢሆንም በነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ምክንያት መሸከም ባለመቻሉ ድጎማውን ደረጃ በደረጃ በማስቀረት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ካለፈው ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮም የታለመለት የነዳጅ ድጎማን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.