Fana: At a Speed of Life!

ኦሮሚያ ክልልና የቻይና ሊያዎኒንግ ግዛት በትብብር ለመሥራት መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል እና የቻይናው ሊያዎኒንግ ግዛት በተለያዩ መስኮች ተባብረው ለመሥራት በበይነ-መረብ መክረዋል፡፡

መድረኩን ያስተባበረው ቤጂንግ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መሆኑን ከኤምባሲው ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ንግድና ኢንቨስትመንት፣ ባሕልና ቱሪዝም እንዲሁም ትምህርትና ጤና በቀጣይ በትብብር የሚሠሩባቸው መስኮች መሆናቸውም ነው የተገለጸው፡፡

የሊያዎኒንግ ግዛት የውጭ ጉዳይ ቢሮ ዳይሬክተር ጄኔራል ሊው ሊ በበኩላቸው፥ በግብርና እና በማዕድን፣ በትምህርትና በጤና እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የሊዮኔንግ ግዛት ከፍተኛ ዕድገት ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ከኦሮሚያ ክልል ጋር በትብብር ለመሥራትም ከፍተኛ ፍላጎት አለን ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

በመድረኩ የኦሮሚያን ክልል እና የሊዮኔንግ ግዛት እምቅ አቅም የሚያሳይ ገለጻ የተደረገ ሲሆን ፥ በቅርቡ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ለመፈራረምም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በውይይቱ ላይ በቻይና የኢፌዲሪ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ የሊያዎኒንግ ግዛት የውጭ ጉዳይ ቢሮ ዳይሬክተር ጀነራል ሊው ሊ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ-መስተዳደር ጽኅፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ኢደኤ እንዲሁም ከሁለቱም ወገን ተጨማሪ ከፍተኛ የቢሮ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ቤጂንግ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ሁለቱን ወገኖች ተቀራርበው እንዲሰሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በማንኛውም ጊዜ እንደሚያደርጉም ነው ቃል የገቡት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.