Fana: At a Speed of Life!

ተቀዛቅዞ የነበረው የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ እየመጣ ነው – ኮርፖሬሽኑ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መቀዛቀዝ አሳይቶ የነበረው የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ እየመጣ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ ከኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡

አቶ አክሊሉ ÷ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (አጎዋ) ከወጣች በኋላ ሌላ የገበያ አማራጮችን በመፈለጓ ተቀዛቅዞ የነበረው የኢንዱስትሪ ፖርኮች እንቅስቃሴ አሁን ላይ ወደ ተሻለ ደረጃ እየመጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መሻሻል የታየውም አምራቾች ቀድሞ በአጎዋ ላይ ተንጠልጥሎ የነበረውን የኢንዱስትሪ ምርቶች ገበያ መዳረሻ ወደ ሌሎች አውሮፓና የምስራቅ ሀገራት ማስፋፋት በመቻሉ ነው ብለዋል።

አጋጣሚውም የኢትዮጵያ ምርቶች በውስን አካባቢ ብቻ ይሸጡ የነበረውን በሰፊው እንዲሸጡ እድልን ፈጥሯል ነው ያሉት።

አሁንም ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ለመሳብና ብዙ አማራጮችን በማስፋት የስራ እድልን ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

በጥላሁን ይልማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.