Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቤቶች ከተውጣጡ መምህራን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ከተውጣጡ ርዕሰ መምህራን፣ ም/ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ዛሬ በአዲስአበባ ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን፣ ም/ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ጋር ፍሬያማ ዉይይት አድርገናል ብለዋል፡፡

በወይይታቸውም÷ በአዲስ አበባ ከተማ ከ557 የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በ18ቱ ትምህርት ቤቶች የተፈጠረው ሁከት የሰው ህይወት ሳይጠፋና የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር እንደተቻለ መገለጹን ነው ያነሱት፡፡

በቀጣይም የመማር ማስተማሩ ሂደት ፍፁም ሰላማዊ እንዲሁም የተረጋጋ እንዲሆን በትጋት እንደሚሰሩ ተሰብሳቢዎቹ እንዳረጋገጡላቸው ጠቅሰዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.