Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ጀርመን ጋር ጠንካራና የቆየ ግንኙነት አላት – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ጀርመን ጋር ጠንካራ እና የቆየ ግንኙነት አላት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

የፈረንሳይ የአውሮፓ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎንና እና የጀርመን የፌዴራል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባየርቦክ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት መግለጫ እየሰጡ ነው።

በመግለጫውም ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ጀርመን ጋር ጠንካራ እና የቆየ ግንኙነት እንዳላት አቶ ደመቀ አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት እና ከሁለቱ ሃገራት ጋር በጋራ የመስራት ፍላጎት እንዳለም ነው የተናገሩት።

የፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበርን በተመለከተ እና ቀጠናዊ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም አንስተዋል።

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ፥ ጀርመን ኢትዮጵያ የጀመረችውን የሰላም ጉዞ ለማገዝ ፈቃደኛ መሆኗን ጠቅሰዋል።

በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንደሚሰሩም ነው የተናገሩት።

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር እንደሚሰሩም አንስተዋል።

የፈረንሳይ የአውሮፓ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎና በበኩላቸው ፥ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላት ቦታ ታሪካዊ መሆኑን አንስተውም ፥ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ሂደትና አፈጻጸም ለማገዝ ፈቃደኛ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

በጦርነት ለነበሩ አካባቢዎች በመሰረታዊ አገልግሎቶች ማስጀመር ላይ፣ በመልሶ ግንባታና ማቋቋም ላይ በተጨማሪም በተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ማጣራት ላይ በጋራ ለመስራት እነደሚፈልጉ ገልጸዋል።

በቀጣይም በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነርን አግኝተው ውይይት እንደሚያደርጉ በጋራ መግለጫው ተነስቷል።

በለይኩን አለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.