Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አመራሮች “ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ተቀላቀሉ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የሆነውን “ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አመራሮች ተቀላቅለዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ንቅናቄውን የተቀላቀሉ ሲሆን÷ የተለያዩ እምነት ተከታዮች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር 1000623230248 ድጋፍ በማድረግ ንቅናቄውን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ንቅናቄው ሰዎች በየመንገድ ዳሩ ከመጸዳዳት ወጥተው ንጽህናውን በጠበቀ ቦታ የመጸዳዳት ባህላቸውን እንዲያሳድጉ ለዚህ ደግሞ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎች እንዲሠሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ መሆኑ ይታወቃል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.