Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሳዑዲ ዓረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፈርሃን ጋር ተወያይተዋል፡፡
አቶ ደመቀ በሳዑዲ ዓረቢያ እየተካሄደ ባለው አይ ኤስ አይ ኤስ የሽብር ቡድንን ለማጥፋት ከተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት የሚኒስትሮች ስብስባ ጎን ለጎን ነው ከሳዑዲ አቻቸው ጋር የመከሩት፡፡
በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
ሀገራቱ በቀጣይ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውንም ሪያድ ዴይሊ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.