Fana: At a Speed of Life!

በናይጀሪያ በተፈጸመ ጥቃት በጥቂቱ 59 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይጀሪያ ምስራቃዊ ክፍል በተፈጸመ ጥቃት በጥቂቱ 59 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ።

ጥቃቱ ቦሮኖ በተባለው ግዛት በምትገኝ ጉዲቦ በተባለች አውራጃ በሚገኝ አነስተኛ መንደር የተፈጸመ ነው ተብሏል።

ለጥቃቱ እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አክራራ ታጣቂ ቡድኖች ሳይፈጽሙት አይቀርም ነው የተባለው።

የአሁኑ ጥቃት ምናልባትም በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ላይ ተወስዷል ለተባለ እርምጃ አፀፋ ሳይሆን እንደማይቀርም ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በግዛቲቱ ቦኮ ሃራምን ጨምሮ ሌሎች አክራሪ ታጣቂ ቡድኖች የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፥ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ቆይተዋል።

ቦኮሃራም እውቅና ካገኘበት የፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ የተለያዩ ጥቃቶችን ያደረሰ ሲሆን፥ ከዚያን ጊዜ ወዲህም በሺዎች የሚቆጠሩትን ለህልፈት ሲዳርግ በርካቶችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በናይጀሪያ እና በቻድ በሁለት ቀናት ውስጥ ባደረሰው ጥቃትም 147 ወታደሮች መግደሉ የሚታወስ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.