Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባውን የኢንሳ ህንጻ መረቁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን አዲስ ህንጻ መረቁ፡፡

ወሎ ሰፈር አካባቢ የተገነባው የዋና መስሪያ ቤቱ ህንጻ ባለ 14 እና ባለ 17 ወለል የሆኑ አምስት ህንጻዎችን ያካተተ ነው፡፡

የህንጻው ግንባታ በ2002 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፥ 2 ቢሊየን 142 ሚሊየን 58 ሺህ 790 ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡

በህንጻዎቹ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ጨምሮ የሰላም ሚኒስቴር፣ የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከልን እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል የሚገለገሉባቸው ይሆናል፡፡

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.