Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና አልጄሪያ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀሪያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከአልጀሪያ የኢነርጂ ማስፋፊያ እና ታዳሽ ሃይል ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሸመስ ኢዴን ሺቱር ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ በሁለቱ አገራት መካከል በታዳሽ ኃይል እና ኢነርጂ ስርጭት ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል፡፡
አምባሳደር ነብያት ኢትዮጵያ የታዳሽ ሃይል የኢነርጂ ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ገልፀው መንግስት የታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ በተለያዩ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ፣ የንፋስ፣ የፀሐይ እና ጂኦ ተርማል የታዳሽ ኃይል ማመንጪያ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታና የድርድር ሂደትን አስመልክቶም አምባሳደሩ ለሚኒስትሩ ገለፃ ያደረጉላቸው ሲሆን ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከታችኞቹ ተፋሰስ አገራት ጋር ያሉትን ልዩነቶች በውይይትና በድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆንዋል ተናግረዋል ።
ሚኒስትሩ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ሀብቶቿን ለማልማት የምታደርገውን ጥረት አልጀሪያ እንደምትደግፍና በዘርፉ ያላትን ልምድ በስልጠናና በአቅም ግንባታ በትብብር ለመሥራት ያላትን ዝግጁነት መግለፃቻን ከአልጄሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በውይይቱ ኢትዮጵያና አልጀሪያ በታዳሽ ኃይል አቅም ግንባታ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት እንዲሁም በሁለቱ አገራት የታዳሽ ኃይል ጉዳይ በሚመለከታቸው ተቋማት መካከል ግንኙነቶችን በማጠናከር የአጋርነት ትብብርን ማድረግ የሚያስችላቸውን ሁኔታዎች ለማመቻቸት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.