Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት ሶስተኛው አስቸኳይ ጉባኤ ነገ በሰመራ ከተማ እንደሚጀመር የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አስታወቁ።
የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አሚና ሴኮ ÷የክልሉ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና በስኬት በተጠናቀቀበት ማግስት የሚካሄድ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
በምርጫው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በስኬት እንዲጠናቀቅ ቁልፍ ሚና ለተጫወቱ በዋናነት ህብረተሰቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የጸጥታ መዋቅሩ የክልሉ ምክር ቤት አክብሮቱ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የተለያዩ የአስፈጻሚ አካላትንተግባርና ሃላፊነት ለመደንገግ የወጡ አዋጆችም ለምክር ቤቱ ቀርበው ውይይት ከተደረገበት በኋላ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።
የአፋር ክልል ምክር ቤት 96 አባላት ያሉትና አስቸኳይ ጉባኤውም የምክር ቤቱ የስራ ዘመን ማጠናቀቂያ እንደሚሆንም ተመልክቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.