Fana: At a Speed of Life!

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 887 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎችና መርሃግብሮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 887ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ከተመረቁ ተማራቂዎች መካከል 55ቱ የሁለተኛ ዲግሪ ምሩቃን ሲሆኑ÷ በአጠቃላይ ከሚመረቁት ውስጥ በኢንጀነሪንግ እና በማህበራዊ ሳይንስ የሚመረቁት ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ።

የሠመራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አደም ቦሪ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት ÷ ኢትዮጵያ አንድም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሌላ በኩል የተለያዩ አለም አቀፍ ጫናዎች እየደረሰባት ባለበት በዚህ ጊዜ ወደ ስራው ዓለም መቀላቀለችሁ ሃላፊነታችሁን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል ብለዋል።

የሠመራ ዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች በሀገሪቱ ለሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በሰከነ ሁኔታ በመመልከት የመፍትሄ ሃሣብ አመንጪ እንዲሆኑ ማሳሰባቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም የሠመራ ዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች በአፋር ክልል በነበራችሁ ቀይታ ከአፋር ህዝብ የተማራችሁትን ሀገር ወዳድነት፣ መተባበርና መደጋገፍ በሄዳችሁበት ሁሉ አንድተገብሩም ጠይቀዋል፡፡

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.