Fana: At a Speed of Life!

የካፋ ዞን 223 ሰንጋዎችን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የካፋ ዞን 223 ሰንጋዎችን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጉን የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው ሃላፊ አቶ መስፍን ተስፋዬ እንደገለጹት÷ከዞኑ ለመከላከያ ሰራዊት በድጋፍ የተበረከቱት ሰንጋዎች ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ ነዋሪዎች የተለገሱ ናቸው።
የዞኑ ህዝብ አሸባሪው ህወሓት ሙሉ በሙሉ እስከሚደመሰስ ድረስ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የካፋ ዞን ህዝብ እስካሁን በሶስት ዙሮች በድምሩ 328 ሰንጋዎችን ለመከላከያ ሰራዊት በድጋፍ ማበርከቱን ነው ሃላፊው የገለጹት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.