Fana: At a Speed of Life!

የደንበኞችን ፍላጎት ማዕከል ያደረገ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን – የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጊዜው የሚጠይቀውን ዘመናዊ የጉምሩክ አስተዳዳር ሥርዓት በመዘርጋት የደንበኞችን ፍላጎት ማዕከል ያደረገ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡

መረጃ እንደሚያሳየው ኮሚሽኑ በ2013 በጀት ዓመት ዓላማውን ለማሳካት በዋና ዋና የትኩረት መስኮች ማለትም በተቋማዊ አቅም ልማት፤ በአሠራር ልህቀት፤ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ልህቀት፤ በህግ ተገዥነት አመራር ልህቀት እና ዘላቂ የገቢ ዕድገት ለማረጋገጥ ውጤታማ  ሥራዎች  ተከናውነዋል።

በዚህም መሠረት በ2013 በጀት ዓመት ብር ከ112 ቢሊየን 462 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ  ለመሰብሰብ ችሏል።

አፈፃፀሙም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው ብር 104.98 ቢሊየን ጋር ሲነፃፀር የብር 7ቢሊየን 48 ሚሊዮን ብልጫ አለው።

በኮሚሽኑ የሥራ ዘርፎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን በመመዘን ከኢትዮጵያ ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ የአገልግሎት ጥራት ማረጋገጫ የዕውቅናና የምስጋና ሰርቴፍኬት ማግኘቱንም መረጃው ይጠቁማል።

በተጨማሪም ለብልሹ አሰራር ተጋላጭ በሆኑ አሰራሮች ላይ ተቋማዊ ስጋት ስራ አመራር ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግና ሌብነትን በመከላከል ተጨባጭ ውጤት በማስመዘገብ ከፀረ ሙስና ኮሚሽን ዕውቅና ማግኘት ተችሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.