Fana: At a Speed of Life!

በከሃዲዎች የተደቀነብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ተዘጋጅተናል- የባሌ ዞን ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሀገሪቱ ላይ የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስ እየተካሄደ ባለው ትግል ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን የባሌ ዞን ወጣቶች አስታወቁ፡፡

ከዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የወጣት ተወካዮች በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በባሌ ሮቤ ከተማ መክረዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት፤ አሸባሪው የሕወሃት ቡድን በሀገር ላይ የፈጸመው ክህደት እጅግ የሚያስቆጭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከውጭ ጠላቶች ጋር በመቀናጀት አሸባሪው ቡድን የከፈተውን ሀገር የማፍረስ ጦርነት ለመቀልበስና ሀገርን ለማዳን እየተካሄደ ባለው ትግል ለመሳተፍ ዝግጁ ነን ብለዋል።

በሀገር ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ሰላምን ለማረጋገጥ በመንግስት የተደረገውን የክተት ጥሪ በመቀበል እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውንም ነው ወጣቶቹ የገለጹት።

ወጣቱ በማህበራዊ የትስስር ገፆች አሸባሪውን ቡድን በሚደግፉ ቅጥረኛ ግለሰቦች በሚነዛው የበሬ- ወለደ ትርክት ሳይዘናጋ የህልውና ዘመቻውን በንቃት እንዲደግፍ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ህወሃት የመላ ኢትዮጵያኖች ሁሉ ጠላት መሆኑን ስለምንገነዘብ ከሌሎች የሀገሪቱ ወጣቶችና የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ለመፋለም ተዘጋጅተናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዞኑ ነዋሪዎች በተለይ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች በሙሉ ወኔና የአሸናፊነት ስነልቦና የህልውና ዘመቻውን ለመቀላቀል በተግባር እያሳዩ ያሉትን ተነሳሽነት አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.