Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እውነታ እና የምዕራባውያን የተዛባ መረጃ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከእውነታ የራቁ መረጃዎችን እያስተላለፉ እንደሚገኙ የደቡብ አፍሪካው ሲቲ ፕረስ በገጹ አስነብቧል፡፡

የህወሓት ሃይሎች የደሴ እና የኮምቦልቻ ከተሞችን ሰርገው በመግባት የተለያዩ የሽብር ድርጊቶችን መፈጸማቸውን ተከትሎ አንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሽብር ቡድኑ አዲስ አበባን ተቆጣጥሯል ሲሉ መዘገባቸውን አስታውሷል፡፡

በዚህም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ የተሳሳተ እና ሆን ተብሎ የተፈበረከ መረጃ እንዲይዙ አድርጓል ይላል ሲቲ ፕረስ፡፡

ሲ ኤን ኤን እና የተቀሩት ደግሞ ጉዳዩን ዝግጅቶቹን በድብቅ ቃላት ሲገልጽ መቆየቱን የሚጠቅሰው ዘገባው ፥ የአሜሪካ ኤምባሲም “አስፈላጊ ከሆኑ ሰራተኞች ውጭ ሌሎች ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ” ማሳሰቢያ መስጠቱን ይገልጻል፡፡

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገና ከጅምሩ ከህወሓት ጎን መቆምን ስለመረጠ ይህ የሚደንቅ አይደለም ሲልም አስነብቧል፡፡

ሆኖም ሁኔታዎች ለህወሓት ሃይሎች ቀላል እንደማይሆኑ ከግንባሩ የሚወጡ መረጃዎችን ይጠቅሳል፡፡

በግንባር ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በተጨማሪ የአማራና የአፋር ሚሊሻዎች እንዲሁም የአማራ ፋኖ ጋር መታገል እንዳለባቸው ጠቅሷል፡፡

በህወሓት የተጀመረው ጦርነት አንድ አመት ሞልቶትም ለተቀረው ዓለም አሁንም ስለኢትዮጵያ የሐሰትእና የተዛባ መረጃ እየደረሰው ስለመሆኑም ዘገባው ያትታል፡፡

ዘገባው አያይዞም ምዕራባውያን ጦርነቱ የተጀመረው የሰሜን ዕዝ ላይ ጭፍጨፋ ከተፈጸመበት በኋላ ባለውና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወታደራዊ ዘመቻው እንዲጀመር ባዘዙበት ዕለት ሳይሆን ከዛ በፊት በነበረው ምሽት ነው በሚል ትክክለኛውን ጉዳይ ችላ ብለውታል ይላል፡፡

በዚህ ወቅትም ከሃዲው ቡድን የትግራይ ተወላጅ ባልሆኑ የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ሌሊት በተኙበት አሰቃቂ ጭፍጨፋ መፈጸማቸውንና ሌሎቹን ማሰቃየታቸውንም ይጠቅሳል፡፡

ህወሓት ከፈጸመው ክህደት ጋር በተያያዘ የህወሓት ጦር መሪ ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይ በሰጠው ቃለ ምልልስ፥ በመንግስት የሚደረግብን ወረራ ለመቀልበስ በማሰብ ጥቃት መፈጸማቸውን ተናግሯል ሲልም ዘገባው ያስታውሳል፡፡

ይህን መሰሉ እርምጃ በምሽት መወሰዱ ያለው ተዓማኒነት ምን ያክል ነው ሲልም ይዞት በወጣው ሰፊ ሃተታ ላይ ይጠይቃል፡፡

በዚሁ እለት ከተፈጸመው ክህደት በኋላም የዕዙ ከባድ መሳሪያዎች መዝረፋቸውን ነው ያስታወሰው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በግልጽ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደርን ማስወገድና የሽግግር መንግስት ማቋቋምን ያካተተ ረጅም ሰነድ በህወሓት በኩል ከተፈጸመው ጭፍጨፋ አንድ ወር ቀደም ብሎ መዘጋጀቱንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

በዕዙ ላይ የተፈጸመው ጥቃትም ህወሓት አዲስ አበባ ለመግባት ያሰበውን ዕቅድ ለማሳካት ያለመ መሆኑን ያነሳው ዘገባው ፥ በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ የቡድኑ ደጋፊዎችም በዚህ ደስታቸውን ሲገልጹ እንደነበነር ማስረጃ መኖሩንም ገልጿል፡፡

ይሁን እንጅ የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን እውነታውን ለዓለም ማሳወቅ አልቻሉም ሲል ይገልጻል፡፡

እነዚህ ሚዲያዎች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ መሆን ጋር በተያያዘ በአሸባሪው ቡድን መንግስት ተገዶ ከገባበት ጦርነት በላይ ምን ዜና አለ ያሉ ይመስላሉ ይላል በዘገባው፡፡

ሆኖም የቀድሞውን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸውን ጠቁሞ፥ በአፍጋኒስታን ያስጀመሩትን ጦርነትም አንስቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በጋራ ባወጡት ዘገባ በህወሓት ሃይልና ተባባሪዎቹ የተፈፀመውን ግፍና በደል በግልፅ አቅርቧል፡፡

ከዚህ በተቃራኒው ግን የምዕራቡ ዓለም ሚዲያ በተለይም ሲ ኤን ኤን ‘‘በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጥምረት የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል’’ በሚል የሰራውን ዘገባ አስታውሶ ፥ የምዕራቡ ዓለም ሚዲያ የተከተሉትን አሉታዊና አፍራሽ መንገድም ዘርዝሯል፡፡

በተጨማሪም በትግራይ ታጣቂዎችና በህወሓት ደጋፊዎች በማይካድራ አማራዎች መጨፍጨፋቸውን ያነሳው ዘገባው፥ የምዕራቡ ዓለም ሚዲያ ግን በአክሱም ከተማ ኤርትራውያን ወታደሮች የትግራይ ተወላጆችን ጨፍጭፈዋል በሚል ተደጋጋሚ ዘገባ መስራታቸውን አንስተዋል፡፡

ዘገባው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች እውነታውን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳዋቀቸውን በማንሳት ጥረታቸውን በማድነቅ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.