ንግድ ባንክ የ2019 የግሎባል ቢዝነስ አውት ሉክ ሽልማትን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትየጵያ ንግድ ባንክ የ2019 የግሎባል ቢዝነስ አውት ሉክ ሽልማት አሸናፊ ሆነ።
የዘርፉን ሽልማት በማሸነፍም ከደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያ ባንኮች በመቀጠል በአፍሪካ ሶስተኛው ባንክ መሆን ችሏል።
ባንኩ በ77 ዓመታት ጉዞው ዓለም ዓቀፍ ሽልማት ሲያሸንፍ የመጀመሪያው መሆኑንም አስታውቋል።
የባንኩ ፕሬዚዳንት ባጫ ጊና ባንኩ ለበርካታ ዓመታት በትርፋማነት መቀጠሉ፣ ተደራሽነቱን ማሳደጉ፣ የደንበኞቹ ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ እና አገልግሎቱን በተሟላ ሁኔታ መስጠት በመቻሉ ሽልማቱን እንዲያገኝ አስችሎታል ብለዋል።
በቀጣይ በተለይም በዲጂታል የባንክ ዘርፍ ጠንክሮ በመስራት ተወዳዳሪ በመሆን ልቆ ለመገኘት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛልም ነው ያሉት።
ሽልማቱ ከባንኩ ጋር በጋራ የሚሰሩ ደንበኞች እና የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
በመለሰ ምትኩ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision