Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ከ3 ቢልየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ3 ነጥብ 2 ቢልየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 64 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የሐረሪ ክልል የኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ለ8 ሺህ 298 ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ 6 ሺህ 8 ወጣቶች በከተማ ግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሀምዲ ሰልሃዲን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ለኢንተርፕራይዞች ከ14 ሚሊየን 206 ሺህ ብር በላይ የብድር አገልግሎት መሰጠቱን ገልጸው÷ የማምረቻና የመሸጫ ቦታን ተደራሽ ከማድረግ አንጻርም 32 ሼዶች ለኢንተርፕራይዞች መሰጠቱን ጠቁመዋል።

ለኢንተርፕራይዞች በብድር የተሰጠ 43 ሚሊየን 787 ሺህ 528 ብር ማስመለስ መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡

የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሽፋንን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን የገለጹት ምክትል ኃላፊው÷ ለ2 ሺህ 466 ተገልጋዮች በኦንላይን አገልግሎት መስጠት መቻሉን አንስተዋል፡፡

ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ከ3 ሚሊየን 999 ሺህ 178 ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉንም ነው የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.