Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአፍዴራ የሚገኘውን የብሮሚን ማምረቻ ፋብሪካን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአፍዴራ የሚገኘውን የብሮሚን ማምረቻ ፋብሪካን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ወቅት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ፋበሪካው አሁን ላይ ወደ ሙከራ ምርት እየገባ መሆኑን ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል።

ፋብሪካው በወር 500 ቶን ምርት ወደ ውጪ መላክ መጀመሩም ተመላክቷል።

ሚኒስትሩ በአፍዴራ እና በሌሎች ሃይቆች ወስጥ የሚገኙ ማዕድናት ወደ ልማት እንዲገቡ ከአፋር ክልል ጋር ጠንክረን እንሰራለን ነው ያሉት።

የሚቀጥሉት አመታት ጉዟችን እውነተኛ የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ እንዲሆኑ እንረባረባለንም ብለዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.