Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ሌላ ማዕቀብ ለመጣል ያላት ፍላጎት አደገኛ መሆኑን የሮኪ ማውንቴይን የሠላምና ፍትህ ማዕከል ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሮኪ ማውንቴይን የሠላምና ፍትህ ማዕከል ÷ በኢትዮጵያ ላይ የሚጣል ማንኛውም ዓይነት ማዕቀብና የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት አደገኛ መሆኑን ገለፀ፡፡

የሠላም እና የፍትህ ማዕከሉ ÷ በኢትዮጵያም ሆነ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ላይ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ኃይል ላይ የተመሠረተ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነትንም ሆነ የኢኮኖሚ ማዕቀብ በጥብቅ እንደሚቃወም ነው ያመለከተው፡፡

ማዕከሉ አሜሪካ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን በፕሮፖጋንዳ እንደምትደግፍ እንዲሁም የቁሳቁስ እና መሠል ድጋፎችን እንደምትሠጥ መረጃ እንዳለው ይጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ቡድኑ በሥልጣን ላይ በነበረባቸው ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የጭቆና አገዛዝን ያሠፈነ መሆኑንም አመላክቷል፤ በመሆኑም አሜሪካ ይሄን እያወቀች ከቡድኑ ጋር ማበሯ አስቆጥቶናል ነው ያለው ማዕከሉ፡፡

በአፍሪካ እና በሌሎች አካባቢዎች የተፈጸመው አስከፊ የምዕራባዊያን የቅኝ ግዛት ታሪክ የአሜሪካንም ሆነ የየትኛውንም ወገን ኃይል ላይ የተመሰረተ ጣልቃ ገብነት ብሎም የኢኮኖሚ ማዕቀብ ለመቃወም ምክንያት እንደሆነም ነው ማዕከሉ የገለጸው፡፡

ማዕከሉ በኮሪያ፣ ቬትናም ፣ ሊባኖስ፣ ሶማሊያ፣ ኒካራጉዋ፣ ሄይቲ፣ ሰርቢያ፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ አፍጋኒስታን፣ በሶሪያ እና በሌሎች ሀገራት ላይ አሜሪካ የወሰደችው የኃይል እርምጃ የከፋ ጉዳት እና አለመረጋጋት እንጂ የሚጠበቀውን ውጤት እንዳላስገኘም አስታውሷል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.