Fana: At a Speed of Life!

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ለመከላከያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ለመከላከያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ12 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

በተለያየ ግንባር የተዋደቁ ጀግኖችን ለሚያክመው የቢሾፍቱ ሆስፒታል ነው የ12 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ልገሳ የተደረገው ፡፡

ድጋፉ በሆስፒታሉ ከቀዶ ህክምና ጋር ተያይዞ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች ፍላጎት በመኖሩ ለዚሁ ግዢ እንዲውል በማሰብ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በርክክብ ሥነ ሥርዐቱ ላይ የተገኙት የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ÷ በቢሾፍቱ ሆስፒታል ውስጥ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ለሚሰሩ የህክምና ባለሞያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይም የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ እንደ መንግስት መስሪያ ቤትም ሆነ ሠራተኞቹ በግል በርካታ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ድጋፉን የተቀበሉት የመከላከያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አመራሮች ስለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.