Fana: At a Speed of Life!

ለባቡር የተዘረጋ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት ሲፈጽሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ለቀላል ባቡር የተዘረጋ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት ሲፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
 
ግለሰቦቹ ከጸሃይ ሪል ስቴት አደባባይ እስከ መሪ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለቀላል ባቡር የተዘረጋ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት ሲፈፅሙ ነው በአካባቢው በነበሩ የፀጥታ አካላት እጅ ከፍንጅ የተያዙት፡፡
 
ተጠርጣሪዎቹ በግምት 3 ኪሎ ሜትር በላይ የሚደርስ የመሬት ውስጥ ተቀባሪ የኤሌክትሪክ ገመድ ሰርቀው በመኪና ለመጫን ሲዘጋጁ በአካባቢው በነበሩ የጸጥታ አካላት አንዱ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት የህግ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ እንዳልክ አንዳርጌ ገልጸዋል፡፡
 
ደርጊቱ የተፈጸመው በተደራጁና ዕኩይ ዓላማ ባነገቡ ግለሰቦች ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ፥ በየጊዜው መሰል ዓላማ ባላቸው ግለሰቦች በኤሌክትሪክ መሰረተልማት ላይ የሚፈጸሙት ስርቆቶች በአገልግሎት አሰጣጡ እንቅፋት እየፈጠሩ ይገኛል ብለዋል፡፡
 
በመሆኑም ሁሉም ህብረተሰብ ከመሰል እኩይ ተግባራት መሰረተ ልማቱ እንዲጠብቅና አጥፊዎችንም ሲያገኝ ከተቋሙ ጋር በመተባበር ለህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ማሳሰባቸውን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በ2006 ዓ.ም የወጣው የኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2006 በማመንጫ፣ በማስተላለፊያ፣ በማከፋፈያና በማሰራጫ ተቋማት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው ከ5 እስከ 15 ዓመት በሚደረስ ፅኑ እስራት ወይም እስከ 50 ሺህ ብር በሚደረስ በገንዘብ መቀጮ ወይም በሁለቱም እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.