Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የህብረተሰቡን ህይወት ለመታደግ ጥረት እየተደረገ ነው – ኢ/ር መሐመድ ሻሌ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በዝናብ እጥረት ምክንያት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የህብረተሰቡን ህይወት ለመታደግ አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ፡፡
 
የሶማሌ ከፍተኛ አመራሮች ከክልሉ ምሁራን ማህበር አባላትና ነጋዴዋች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ እና በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ውይይት አካሂደዋል ።
 
ውይይቱ ምሁራኑ ሀገሪቱና ክልሉ ከሚገኙበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ማድረግ በሚገባቸው ተሳትፎና በሚኖራቸው ገንቢ ሚና ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
የውይይት መድረኩን የመሩት የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሀገሪቱና በህዝቡ ላይ የፈፀመው በደል እና ክህደት በታሪክ ያማይረሳ መሆኑን ገልፀዋል።
 
በክልሉ በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ምህዳርን ለማስፋት በተሰራው ስራ በክልሉ የሚገኙ ምሁራን እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሐሳብን በነፃነትና በሰለጠነ መንገድ እንዲያራምዱ ምቹ ሁኔታን መፈጠሩን ጠቁመዋል፡፡
 
በክልሉ በዝናብ እጥረት ምክንያት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የህብረተሰቡን ህይወት ለመታደግ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ መሆኑን ኢንጂነር መሐመድ አረጋግጠዋል፡፡
 
በዚህ መሰረትም የምግብ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃና የእንስሳት መኖ አቅርቦትን ለማህበረሰቡ የማዳረስ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
 
ድርቁ በህብረተሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በሚደረገው ጥረት የክልሉ ምሁራንና ነጋዴዋችም የበኩላቸውን ሚና እንደወጡ ጥሪ ማቅረባቸውንም የሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.