Fana: At a Speed of Life!

የወሰን ማስከበር ችግር የቃሊቲ ቶታል አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ  የመንገድ ግንባታ ላይ ጫና አሳድሯል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሰን ማስከበር ችግር  የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ አስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ጫና ማሳደሩ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የሚያስችሉ የውስጥ ለውስጥና አቋራጭ መንገዶችን እየገነባ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ አስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

አሁን ላይም   2 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የሚሆን የአስፋልት ማልበስ ስራ፣ ሰብ ቤዝ ፣ ድጋፍ ግንብ፣ የፓይፕ ቀበራ ፣ የእግረኛ መንገድ እና ተያዥ ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ነው የተባለው፡፡

መንገዱ  በታቀደለት ግዜ ገደብ እንዳይጠናቀቅ   የወሰን አለመከበር ማነቆ መሆኑም  ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

በህዳር 2011 ዓ.ም  የተጀመረው ይህ የአስፋልት መንገድ  ፕሮጀክት 5 ነጥብ 6  ኪሎ ሜትር አጠቃላይ ርዝመት ሲኖረው  25 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.