Fana: At a Speed of Life!

በ”ታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ” መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እንግዶችን ለመቀበል የተቋቋመው ኮሚቴ ዝግጅቱን አጠናቋል – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ”ታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ” መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እንግዶችን ለመቀበል የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አንድ ሚሊየን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።

በዚህ መሰረትም በ”ታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ” ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ለማስተናገድ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ብሔራዊ ኮሚቴው በጥሪ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዳያስፖራዎችን ለማስተናገድ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።

በሀገራዊ ጥሪው አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ ላሳዩ በሙሉ የሰጡትን ታላቅ ምላሽ እናደንቃለንም ብለዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.