Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና ፖሊስ በግንባር እየተፋለሙ ለሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አባላት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና የድሬዳዋ ፖሊስ ግንባር ላይ እየተፋለመ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አበረከቱ።
የፌደራል ፖሊስ ሰራዊት ከመንግስትና ከህዝባችን የተሰጠውን አደራ በመቀበል የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ ለመግታት በኦሮሚያ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ በመተከል፣ በካማሺ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ተናግረዋል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በበኩላቸው÷ እኛ እያለን ሀገር አትደፈርም ብሎ ለውድ ህይወቱ ሳይሰስት በጀግንነት በመታገል የሽብር ቡድኖቹ ሽንፈት እንዲከናነቡ ላደረገው ሠራዊት ትልቅ ክብር ይገባል ብለዋል።
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽነር አለሙ መግራ እንደገለጹት፥ ሀገርን በጀግንነት መጠበቅና ህዝብን በሰብዓዊነት ማገልገል ትልቅ ክብርና እድለኝነት ነው።
በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሀር የተመራው ልዑክ 45 ሰንጋዎችን፣ የምግብ እቃዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ የድሬዳዋ ፖሊስና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በግዳጅ ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላትንም በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል ተገኝተው ማበረታታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.