Fana: At a Speed of Life!

ለሰራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ የተሰጠንን ግዳጅ በጀግንነት እንድንወጣ መነሳሳትን ይፈጥራል – ሜ/ጄ ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋና አዛዡ ይህን ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አብሮ አደግ ጓደኛማቾች ያሰባሰቡትን ግምቱ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የእርድ ሰንጋዎችንና የታሸገ ውሃ ድጋፍ በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በተረከቡበት ወቅት ነው።
ኢትዮጵያ ታላቅ ሃገር በመሆኗ ለታላቅ ሃገር የሚሚጥን አየር ኃይል እየተገነባ እንደሚገኝ የገለፁት ጄነራል መኮንኑ÷ እየተዋጋንም ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በማከናወን ምቹ የስራና የመኖሪያ ቦታን ለመፍጠር በሰራዊቱ ጉልበትና የተለያዩ ተቋማትን በማስተባበር በርካታ ስራዎች በመከናወን ላይ እንዳሉ ተናግረዋል ።
ህዝባችን እያደረገ ያለው ድጋፍም የተሰጠንን ግዳጅና ተልዕኮ በታላቅ ሃገራዊ ወኔና ጀግንነት እንድንወጣ ያስችለናል ብለዋል።
የክፍለ ከተማው አብሮ አደግ ጓደኛማቾችም ላደረጉት ድጋፍ በተቋሙና በሰራዊቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ድጋፉን ያበረከቱት የክፍለ ከተማው አብሮ አደግ ጓደኛሞች ተወካዮች አቶ ነጋሽ ዳዲ እና አቶ ሄኖክ አበበ በበኩላቸው፥ ተቋሙ ከህልውና ዘመቻው በተጓዳኝ አየር ኃይሉን በዘመናዊ መልኩ ለመገንባት እየተደረገ ባለው ጥረት ኩራት እንደሚሰማቸው ገልጸዋል።
አያይዘውም መስዋዕትነት በመክፈል ሃገራችንን በጀግንነት እየጠበቀ ለሚገኘው ጀግናው ሰራዊታችን የሚያደርጉትን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.