Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በሰቆጣ ከተማ የሚገኙ ተቋማትን አውድሟል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ በቆየባቸው ጊዜያት የዋግ እና አካባቢው ህዝብ ብቸኛ ተቋም የሆነውን የሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅን ጨምሮ በርካታ መሰረተ ልማቶችን አውድሟል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በቦታው ተገኝቶ እንደተመለከተው÷ ኮሌጁ ሙሉ በሙሉ ወድሟል፣ የተማሪዎች ሬጅስትራር ክፍል መረጃ ተዘርፏል፣ ዳግም አገልግሎት እንዳይሰጥ ተደርገው ጠቃሚ የሚባሉ ዕቃወች ሁሉ ተዘርፈዋል።
በተቋሙ ያሉ አገልግሎት የሚሰጡ ኮምፒውተሮች እና ሌሎች ቁሳቁስ ከፎቅ ላይ ወደ ምድር እንዲጣሉ ተደርገው ተሰባብረዋል፡፡
የሁሉም ኮምፒተሮች ሃርድ ዲስክ በቡድኑ ተወስደው፥ በቤተ መፅሃፍቱ የነበሩ መፅሃፍትም ወድመዋል፡፡
የተማሪዎች መመረቂያ ጋወን በየቦታው ወድቀው እንዲረጋገጡ ተደርገዋል፣ ከተለያዩ ሃገራት በስጦታ የተገኙ የሙዚቃ መሳሪያዎች ተዘርፈዋል፣ ቡድኑ መውሰድ ያልቻለውን ደግሞ ሰባብሮ እንደጣላቸው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባልደረባ በስፍራው ባደረገው ቅኝት መታዘብ ችሏል።
የመሰብሰቢያ አዳራሾች በሚያፀይፉ ስድቦች እና ቃላት ተሞልተው፥ የዋግ ህዝብ መገልገያ የሆኑ በርካታ ተቋማት መዘረፋቸውን እና መውደማቸውን ጣቢያችን ተመልክቷል፡፡
በምንይችል እዘዘው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.