Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የሐረማያ ሐይቅን አፀዱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ባዘጋጀው የፅዳት ዘመቻ ላይ ተመራቂ ተማሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ የከተማው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
ሐይቁን የመንከባከብ ስራ ጊዜን ጠብቆ ብቻ መሆን እንደሌለበት የገለጹት ተመራቂ ተማሪዎቹ፥ የፅዳት ዘመቻን ዘላቂነት ያለው ለማድረግ ሁሉንም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አካላት ባሳተፈ መልኩ ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የቴክኖሎጂው ኢኒስቲትዩት የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ተማሪ አሚር አብዱልአማን በበኩሉ፥ የሐረማያ ሐይቅን መንከባከብ ለነገ የማይባል ተግባር ነው ብሏል።
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችም ሐይቁን በዘላቂነት ለማቆየት በሚደረገው ጥረት ውስጥ እያበረከቱት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሶ፥ ተሳትፏቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችም የምረቃ ቀናቸው መቃረቡን አስመልክቶ የፅዳት ስራ ማከናወናቸውን ገልጸዋል።
ይህንን የተማሪዎች መነሳሳት በመጠቀም በቀጣይ መጠነ ሰፊ ስራ ይሰራልም ተብሏል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.