Fana: At a Speed of Life!

በ”አንድ ብር ለሠብዓዊነት” 120 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ ያለመ መርሃ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በመዘዋወር ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚውል 120 ሚሊየን ብር ማሰባሰብን ዓላማ ያደረገ “አንድ ብር ለሠብዓዊነት” የተሰኘ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ተጀምሯል።

መርሃግብሩ ስለ ፍቅር ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ጋር በመተባበር የሚያካሂደው ነው ተብሏል።

ሕዝቡን በማስተባበርና ከአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ጋር በመሆን በመዲናዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ይካሄዳል ሲሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል አጥናፉ በሰጡት መግለጫ አመላክተዋል፡፡

ከእምነት ተቋማት፣ ከትምህርት ቤቶች፣ ከመንግሥትና ከግል ተቋማት እንዲሁም ከተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር ለመሥራት መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።

ኅብረተሰቡ በአገሪቷ ወቅታዊ ሁኔታ ለተጎዱና ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ከአንድ ብር ጀምሮ ያለውን በመለገስ ተሳትፎ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

ስለ ፍቅር ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት በተለይ በጎዳና ተዳዳሪዎችና በሴቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.