Fana: At a Speed of Life!

ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የደንና የመሬት ገጽታ ማገገሚያ መርሀ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የደንና የመሬት ገጽታ ማገገሚያ መርሀ ግብር ይፋ ሆነ፡፡
የግብርና ሚኒስቴር፣ ዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ልማት ኢኒስቲትዩትና ኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በጋራ የሚተገብሩት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የደንና የመሬት ገጽታ ማገገሚያ መርሀ ግብር ይፋ ሆኗል።
በተመረጡ የተፋሰስ አካባቢዎች የተራቆተ መሬት መልሶ እንዲያገግም የማድረግ ዓላማ ያለው መርሃ ግብሩ የማስፈጸሚያ 9 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ተመድቦለታል ተብሏል።
ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚተገበረው ይህ መርሃ ግብር የማስፈጸሚያ ወጪውን የሚሸፍነው የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.