Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት ለመከላከያ ሰራዊት እና ተፈናቃዮች ከ67 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት እና በአሸባሪው ህወሓት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋሚያ ከ67 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል ።
 
በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ 46 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ፣ የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ኤጀንሲ 20 ሚሊየን ብር እንዲሁም የቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት የ1986 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የ 500 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
ድጋፉን የተረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ÷ እንደ አገር የተቃጣብንን የህልውና አደጋ በመቀልበስ ረገድ መላው የጸጥታ ኃይል ላሳየው ጀግንነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
የአዲስ አበባ ከተማ ማህበረሰብ ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሃብት በማሰባሰብ ለመከላከያ ሰራዊትና በአሸባሪው ህወሓት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ላደረጉት ድጋፍም አመስግነዋል፡፡
 
አቶ ጃንጥራ ሴረኞች በከፈቱብን ጦርነት እንዲደቅ የተደረገውን ኢኮኖሚ እንደገና የመገንባት እና የተፈናቀሉ ወገኖችን በገንዘብና በሃሳብ መርዳት ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር ነው ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.