አሜሪካ በጃፓን በለይቶ ማቆያ የነበሩ ዜጎቿን ለተጨማሪ ምርመራ ከጃፓን አስወጣች
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ በተከሰተባት የጃፓኗ ዲያመንድ ፕሪንስ መርከብ ውስጥ የነበሩ ዜጎቿን ከጃፓን አስወጣች።
በመርከቧ ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የያዙ ሁለት አውሮፕላኖችንም ወደ 400 የሚጠጉ ሰዎችን ይዘው አሜሪካ ደርሰዋል።
3 ሺህ 700 ሰዎችን የያዘችው ዲይመንድ ፕሪንስ መርከብ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ለሳምንታት በዮኮሀማ እንድትቆይ ተደርጓል።
በመርከቧ ውስጥ ከነበሩ መንገደኞች መካከል 400 ያክሉ አሜሪካውያን እንደነበሩም ተገልጿል።
አሜሪካውያኑ ያለፉትን ሁለት ሳምንታት በለይቶ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ ተደርገዋል።
ከተመላሾቹ ውስጥ 14ቱ በተደረገላቸው ምርመራ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ነው የተባለው።
በጃፓኗ መርከብ 99 አዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች በዛሬው እለት ሲገኙ፥ አጠቃላይ የቫይረሱን ተጠቂወች ቁጥር ወደ 454 ከፍ አድርጎታል።
ይህም ከቻይና ውጭ የተመዘገበ ከፍተኛው የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ያደርገዋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision