Fana: At a Speed of Life!

ተመራቂ ሃኪሞችን ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር አዳዲስ ምሩቃን ሃኪሞችን በቅጥር ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል የፕሮጀክት ስምምነት ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች ጋር ተፈራረመ።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ፕሮክጀቱ በብዙ ልፋት ተመርቀው ስራ ላይ ያልተሰማሩ ሃኪሞችን ወደ ስራ የሚያሰማራ በመሆኑ በጤናው ዘርፍ ትልቅ እምርታ ነው ብለዋል፡፡

ከተያዘው አመት ጀምሮ የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት የሶስት ዓመት ቆይታ እንደሚኖረው የጤና ሚኒስቴር መነረጃ ያመላክታል።
በመጀመሪያው ዓመት 2 ሺሕ 898 ሃኪሞችን ወደ ስራ ለማሰማራት መታቀዱን ገልጸዋል።

ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው በጀትም የመጀመሪያው ዓመት ከፌዴራል መንግሥት እና ከአጋር ድርጅቶች በተገኘ ገንዘብ የሚሸፈን ሲሆን፥ ሁለተኛው እና ሶስተኛው ዓመት ከፌዴራል፣ ከክልልና ከከተማ አስተዳደሮች እና ከአጋር የልማት ድርጅቶች ድጋፍ በተገኘ ገንዘብ የሚተገበር ይሆናል።

ከአራተኛው ዓመት በኋላ ሙሉ በሙሉ በክልሎች አቅም እንደሚተገበርም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.