Fana: At a Speed of Life!

በጸጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ከጥር 24 እስከ 27 ይወስዳሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 የጸጥታ ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ከጥር 24 እስከ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ፈተናው እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
 
በሁለተኛ ዙር የሚሰጠውን ፈተና 58 ሺህ 936 ተማሪዎች እንደሚወስዱም የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ተናግረዋል።
 
በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በፀጥታ ምክንያት ፈተና መወሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ አቶ ተፈራ አብራርተዋል።
 
የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ሁለተኛ ዙርም በሰላም እንዲጠናቀቅ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
 
ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት ፈተናው በሰላም መጠናቀቅ እንዲችል የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.