Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል 146 ግለሰቦች ተፈቱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣  2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከልል ከሀገር ህልውና ማስከበር ዘመቻ ጋር ተያይዞ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከአሸባሪው ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 146 ግለሰቦች የተሀድሶ ስልጠና ተሰጥቷቸው ተለቀዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5 /2014  መሰረት የሽብርተኛው ሕውሃት እና የሽብር ግብረ-አበሮቹ እንቅስቃሴ ደጋፊና ፈጻሚ እንደሆኑ ተጠርጥረው ተይዘው የነበሩ ተጠርጣሪዎች የምርመራ ቡድኑ እና የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በሰራው ስራ ለሀገር ስጋት አይሆኑም ተብለው የተለዩትን የመጀመሪያ ዙር 146 ተጠርጣሪዎች ኮማንድ ፖስቱ እንዲፈቱ ወስኗል ተብሏል።

በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተጠርጥረው የተያዙ ሌሌች ተጠርጣሪዎችም በየደረጃው ጉዳያቸው ተጣርቶ ሰላማዊ መሆናቸው ሲረጋገጥ በቀጣይ እንደሚለቀቁ መገለጹን ከክልሉ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.